Monday, December 3, 2012

የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ!!!

በበላይ ወንዳፍራሽ

ይህ ወቅት በሃገራችን ኢትዮጵያ አንዳች ለውጥ ሊመጣ በዋዜማው ላይ እንገኛለን።ይሁን እንጂ ይህ የለውጥ ዋዜማ በሁለት ተፃራሪ ኃይሎች የስንግ ተይዞ በአንድ በኩል ለዴሞክራሲ መወለድ
የሚያምጡትን ያህል በሌላ በኩል የህዝባችንን የሰቆቃ ዘመን ለማራዘም በወያኔ ተላላኪነት እና ጉዳይ አስፈፃሚነት ቀን ከሌሊት በጥቅም ታውረው የሚታትሩ እንዳሉ ይታወቃል። ለዚህም በተለምዶ
"የዳያስፖራ ፖለቲካ" በመባል የሚታወቁት ከኢትዮጵያ ውጪ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ እና ድጋፍ
ሰጪ ድርጅቶች የዚሁ የወያኔ ቅጥረኞች የቀጥታ ሰለባ ሲሆኑ በተለይ በቅርቡ የግንቦት-7 ለሁለት
መከፈል በአይነቱ የሚጠቀስ ሲሆን ሌላው ሰሞኑን በሁለት ገቢር ተከፍሎ  በኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንባር ላይ ያነጣጠረው አሳፋሪም አስቂኝም ድራማ ነው።ስለሆነም እነዚህን ባለሁለት ገቢር
ድራማዎች በጥልቀት ማየቱ ረጅሙ የወያኔ እጅ ምን ያህል ተኩላዎችን የበግ ለምድ እያለበሰ
በውስጣችን እንደሰገሰገ ለማሳየት ይረዳል።

ገቢር-አንድ
ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በተፃፈ ደብዳቤ ከድርጅቱ በስነ-ምግባር የተባረሩ ስደተኞችን
በማሰባሰብና ከጀርባ በመሆን የሃሰት ክስና የስም ማጥፋት ዘመቻ በአመራሮቹ ላይ በሰፊው እንዲደረግ
ከፍተኛ ሚና በመጫወት የመጀመሪያውን ያልተሳካ ሙከራ ያደረገው የወያኔና የሻዕቢያ ተላላኪው አቶ
በላይነህ ወንዳፍራሽ የሚባል ግለሰብ ሲሆን በአደባባይ የወያኔን መንግስት የሚቃወም ቢመስልም
በተግባር የታየው ግን ያለምንም ችግር ኢትዮጵያ የሚመላለስ ከመሆኑ ባሻገር ከስደተኞች በሚዘርፈው
ገንዘብ አዲስ አበባ ውስጥ በልጁ ስም የመድሃኒት ማከፋፈያ ድርጅት እንዳለው ይታወቃል። ከዚህም
ባሻገር ይህ ግለሰብ በጀርመን ሀገር የሲቪክ ማህበር አቋቁሚያለሁ እያለ በአንድ በኩል ከተሰማራበት
የሽንት ቤት ማፅዳት ስራ ከሚያገኘው ገቢ ታክስ እንዳይቀነስበት የዕርዳታ ድርጅት አቋቁሜ ስደተኞችን እየረዳሁ ነው በሚል ለምክንያትነት የሚጠቀምበት ሲሆን በሌላ በኩል ከስደተኞች ገንዘብ
ለመዝረፊያ ይጠቀምበታል።

ጥቂት ስለ ሲቪክ ማህበሩ
ይህ ራሱን የሲቪክ ማህበር እያለ የሚጠራ ድርጅት በላይነህ ወንዳፍራሽ  በሚባል ግለሰብ የሚመራ
ሲሆን ይህ ግለሰብ ከዛሬ 5 ዓመት በፊት ማለትም የአርበኞች ግንባር ከኤርትራ ከመውጣቱ በፊት
ከዳያስፖራ ለጋሽ ግለሰቦች ለግንባሩ የተሰበሰበውን 37000.00 ዩሮ ´´ቁማር ተበላሁ´´ በሚል ተልካሻ
ምክንያት ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ ያዋለ ሲሆን ዛሬም ይህ የማጭበርበር ተሞክሮ አድማሱን በማስፋት
በስደተኞች ላይ የሚያደርገውን ዘረፋ በሚከተሉት መልኩ እያከናወነ ይገኛል።

1. ሰላማዊ ሰልፎችን በማዘጋጀት ለስደተኞች ማመላለሻ በሚል ከለጋሽ ድርጅቶች አውቶብሶችን
በነፃ ከተረከበ በኋላ እያንዳንዱን ስደተኛ ለትራንስፖርት 20.00 ዩሮ እና ከዛ በላይ
እንዲከፍሉ ማስገደድ።

2. ከአሜሪካና ከካናዳ የተጋበዙ እንግዶች የሚመሩት ስብሰባ ስላለ በሚል ስደተኞችን ከየከተማው
እንዲሰበሰቡ ካደረገ በኋላ ከካሪታስ በስደተኞች ስም በነፃ ለተፈቀደለት አዳራሽ የመግቢያ እና
የአዳራሽ ኪራይ ክፈሉ እያለ ስደተኞችን ለተጨማሪ ወጪና እንግልት መዳረግ።

3. ለስብሰባዎችም ሆነ ለሰላማዊ ሰልፎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ልስጣችሁ በሚል በነፍስ
ወከፍ 1.50 ዩሮ ክፈሉ እያለ ስደተኞችን ማንገላታትና መበዝበዝ ይገኝበታል።

ገቢር-ሁለት /ኦክቶበር 20,2012/
 "አፉ ከእኛ፤ልቡ ከነኛ"
ይህ ድራማም የተፈፀመው በበላይ ወንዳፍራሽ በሚመራውና  በጀርመን ሀገር በሚገኘው ከማንኛውም
የፖለቲካ አመለካከት "ነፃ" የሆነ አቋም አለኝ በሚለው ማህበር ሲሆን ይህ ማህበር ፈቃዱን ሲያገኝ
በተለይ ስደተኞችን "አገለግላለሁ" በሚል እሳቤ ቢሆንም ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የስደተኞችን
ገንዘብ መበዝበዣ ሆኖ የሚያገለግል ድርጅት ነው።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ማህበር ምንም እንኳን
በኢትዮጵያውያን ስም የተመሰረተ ቢሆንም ኦክቶበር 20,2012 ቀን "እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንባር በሻዕቢያ ቁጥጥር ስር ያለው ስለሆነ ኑ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ላረጋግጥላችሁ" ሲል
ስብሰባ ጠራ።ከዛ በፊት ግን ለግንዛቤ እንዲረዳ አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በርግጥም በአንድ ወቅት በኤርትራ ምድር ላይ ይንቀሳቀስ የነበረ
ቢሆንም በሚከተሉት ጠንካራ ምክንያቶች ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ከጥቂት የሻዕቢያ ጉዳይ
አስፈጻሚዎች በቀር ሙሉ በሙሉ ከኤርትራ ለቆ ወደበረሃማው ሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ወርዷል።

   1. ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የማይቀየር አቋም፦ ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያለው
አቋም ዛሬ እንደአዲስ የሚነሳ ሳይሆን "የመቶ አመት የቤት ስራ" በወያኔ በኩል የሰጠን
ቢሆንም ከአመታት በኋላ ቀርበን ብናየውም ይህ አቋሙ ምንም ያልተቀየረ ሲሆን በተለይ
እንደየኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አይነት አንድነትን የሚሰብኩ ድርጅቶች ተጠናክረው
እንዳይወጡ በመከላከል ይልቁንም ስር-ነቀል ለውጥ ከማምጣት ይልቅ በወያኔ ላይ ትንኮሳዎችን
በማድረግ ብቻ ወያኔን ከመጣል ይልቅ በመተንኮስ ላይ ብቻ እንድናተኩር ጫና በማድረጉ።  

2. ሻዕቢያ በእጅ አዙር ሊጠቀምብን በመፈለጉ፦በእርግጥም ሻዕቢያ ከመሰረታዊው
የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሱን ጦርነት በእጅ አዙር /Proxy War/ እንድንዋጋለት
በመፈለጉ እና ይህንንም በተቃወሙ አባሎቻችን ላይ የሞት እርምጃ በመውሰዱ ነው።
ወደጥንተ ነገራችን ስንመለስ የጀርመኑ "የሲቪክ" ማህበር ነው እንግዲህ በሻዕቢያ ቁጥጥር ስር
የሚገኘውን ቡድን በኢትዮጵያ ለምድ በመሸፋፈን ለኛ ለኢትዮጵውያን እንደመርገም ጨርቅ የሆነውን
የሻዕቢያ አርማ ከፍ አድርጎ ያውለበለበው።
በእርግጥ መለስ ዜናዊ ሲሞት ከወያኔ እኩል ለቅሶ የተቀመጠው ሻዕቢያ መሆኑን ላስተዋለ የወያኔ እና
የሻዕቢያ "ቅራኔ" "አህያ ቢራገጥ…….". እንደሚባለው ነውና በሻዕቢያ አጋፋሪነት የኢትዮጵያ ህዝብን
ጥቅም አስከብራለሁ ማለት ዘበት ነው።እናም ይህ "የሲቪክ" ማህበር ነው እንግዲህ በሻዕቢያ ሳምባ
እየተነፈሰ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርን "ለማስታረቅ" ብሎም ለመምራት ኃላፊነቱን ስጡኝ
ሲል የደፋር ድፍርስ አይኑን እያቁለጨለጨ የጠየቀው።
"ለራሱ አያውቅ ነዳይ፤ቅቤ ለመነ ለአዋይ" እንዲሉ!!!

ዘገየ አለምሰገድ ከበደ
ከስሽቱትጋርት

No comments:

Post a Comment