Saturday, August 8, 2015

የወያኔ ግፍ በ ሙስሊሙ መህበረስብ - አርበኛ ሰኢድ ሸልመው

የወያኔ  ግፍ በ ሙስሊሙ  ማህበረስብ  !

------

በተጨባጭ ሽብር  ሳይኖር ጠንካራ  የሽብር  ህግ ያላት ሀገራችን  በተለይም  የፀረ ሸረብር  አዋጁ ከወጣ  ከ

2003 ጀምሮ ዜጎች  ወደ እስርቤት  ምክኒያት እየተፈለገባቸው ፣   ዜጎች ጎርፍዋል ፣ ለ አብነት  ለመጥቀሰ

የኦሮሞኛ ቋንቋ  ተናጋሪ  ፣ የ አማርኛ  ቋንቋ ተናጋሪ  ህዝቦች  ላይ  የሚደረሰው  ሰብአዊ  ጥስት መጥቀስ

የችላል  ፣ ይህንንም  አይተው ዝም  ያላሉቱን  ጋዜጠኞች  እና ፀሃፊያን  ፣ ጦማሪያን  ማሰሩን  ወያኔዎች

ተያይዘውታል   ።

በተጨማሪም  የወያኔ ፀረ ሽብር  ኣዋጅ  ለ ጋዜጠኞች እና ለነፃው ፕሬስ ብቻ አይደለም ደንቃራ  የሆነብን   ።

 በተለያዩ እመነት  ተቋማት ምእመናን  በመንግስት  ከ ሚመደብላቸው ካድሬ የእመነት  መሪዎች  የወያኔን ፖሊሲ

እና መመሪያ ከመተግበር  እስከ  የ እምነት  ህግ እና ደንብ  እሰከመጣስ ደረጃ የሚደርሱት  እነዚህ  አድር

ባዮች  ምእመናኑን አሳልፈው  ሽጠውታል  ።  ለዛም  ነዉ ሙስሊሙ ማህረሰብ   ድምፃችን  የሰማ  በማለት  ለ

ገዢው  ፓርቲ  በተደጋጋሚ  በ ዴሞክራሲያዊ  ወይም እነሱ  እንደሚሉት   በ ህገ መንግስቱ  የፀደቀላቸውን

መብት  ነው ጥያቄ ያቀረቡት   ሆኖም  ግን  የጫካ ህግ የሚቀናው ጎጠኛው የ ወያኔ ቡድን      የ ምእመናኑን

ጥያቄ  ከመቀበል  እና  ህገ መንግስታዊ   መብታቸውን ከማሰከበር   ይልቅ   ፣ ላለፉት  3 አመታት  በ

ሙስሊሙ  ማህበረሰብ ላይ  ከፍተኛ  የሰብአዊ  ጥሰት  ሲያደርግ  ቆይቷል ።

የሙስሊሙ  ማህበረሰብ   ከ 2003 አመት  ጀምሮ  ከፍተኛ  ሰቅይ እና በደል  በምእነት ተከታዩ  ላይ በወያኔ

መንግሥት ደርሶበታል ።

ለአብነት ለመጥቀስ ፣ በኮፈሌ፣በገርባ ፣ በ አዲስ አበባ አወሊያ እና በ 2005  በአዲስ  አበባ ለ ኢድ ሰላት

 በተሰበሰበው  ምእመናን ለይ መንግስት በወሰደው እርመጅ ፣ ንፁሃን ታስረዋል ተደብድበዋል ፣ ተገድለዋል ።



የ ሙሰሊሙ  መፈትሄ  አፈላላጊ ኮሜቴ  ምንድን ነው አለማው  ?  በ ማንሰ ተወከለ አመራረጡስ  ?



የአወሊያን ተቋም እና የህገ ወጡ መጅሊስ ብሎም መንግሥት   በግዳጅ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ሊጭን ያሰበውን

የአህባሽ አስተምህሮት  በመቃወም ህዝበ  ሙስሊሙ  በ ጁማአ እለቶች በ አወሊያ ከስግደት ቡኃላ  ድምጻችን ይሰማ

በደላችንን መንግሥት  ይመልከት  በሚል በ ዴሞክራሲያዊ እና ፍፁም ሰላማዊ  በሆነ መንገድ  ያቀርብ ነበር

። ስለሆነም በ ምእመናኑ ምርጫ  ይህን ጥያቄ  ለ መንግሥት  አካላት ጋር ሄደው ሊያቀርቡ የሚችሉ ግለሰቦችን

በፍቃደኝነት  እንዲመርጥ ተደረገ ፣ እነዚህ  17 ኮሜቴ አባላት በተለያዩ  የስራ መሰክ ያሉ እና በሙያቸው

ጥያቄዎችን  ለመንግስት  ለማቅረብ  ብቃት አላቸው  ብሎ ህዝቡ የወከላቸው ናቸው   ፣ በወቅቱ እነ ዶር ሽፈራው

ሚኒስትሩ  ሳይቀሩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ   ዴሞክራሲያዊ እና  ሰለማዊ መሆኑን የመሰከሩለት ነበር ፣ በ

ሂደት ግን መንግሥት  ለሰላማዊ  ዴሞክራሲያዊ  ጥያቄዎች  መለስ ከመሰጠት ይልቅ እስር እና ድበደባ ነበር በ

ህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለይ ያደረገው  ፣ ህገ መንግሥታዊ  መብታቸው  ለማሰከበር  ጥያቄዎችን ባቀረቡ

ኮሜቴው  እና ብዛት ያላቸው  ምእመናን  ለ እስር ተዳረጉ   መንግስት  በ ኢቲቪ ቴሌቪዥን  ጣቢያ  አቅርቦ

ቃለ መጠይቃቸውን በመቆራረጥ እና  በካቴና አስሮ ቃለመጠይቅ  ያደረጋቸውን  በማቅረብ ፣  ሽብር ሲያሴሩ

አገኘናቸው  በሚል የውሸት  ድራማ  ሰራባቸው ፣  እናውቃለን  ወያኔ በድራማ  የተካኑ መሆናቸውን ለአብነት

ለመጥቀስ የ ስውዲን ዜግነት ያላቸውን ጋዜጦች  ከ ኦብነግ ነፃ አውጪ ወታደር  ጋር ሲዋጉ  አገኞሃቸው ካለ

ቡኃላ የወያኔ ድራማ ታአማኚነትን አጥቶል   ። በሙስሊሙ መፍትሄ  አፈላላጊ  ኮሜቴ   የተደረገው ሐቅ ከዚህ

አይለይም ።



መሰመር ያለበት  ጉዳይ የኮሜቴው አባላት የተወከሉት  በ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በ ፍቃድኘት  ከተሰበሰበው

ምእመናን ጥቆማ ነው ።  እኔ

እዚህ ላይ  የመሳጣቹ  ምስክርነት  ፣ የ ሰማሁትን አልያም የነብብኩትን አይደለም    በወቅቱ እኔም በቦታው

ተገኝቼ  ስለነበር  የአይን ምስክርነት  ጭምር  ነው ።



የ ኮሜቴው የፍርድ ሂደት  !



ለአለፉት 3 አመታት ባየነው  የፍርድ ቤቶች   ውሎ  ኢትዮጵያ ወስጥ ፍርድ የሚሰጠው ከ መጋረጃው  ጀርባ ባሉ

ካድሬዎች ወስኔ  መሆኑን የታዘብነበት አጋጣሚዎችን ነው    ፣ ለ ዛም ነው ኢትዮጵያ ውስጥ  ወያኔዎች  ዜጋን

እንደፈለጋቸው ያስራሉ ሲፈልጉ እንደፈለጋቸው ይለቃሉ  ከ 15 ቀን በፊት የተደረገው  ጦማሪያኑ   ከ እስር

ሲፈቱ

 ያየነው ይህን ነው ። ከ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ   እንደ ቀልድ ነፃ  ናቹ እቃቹሁን አዘጋጁ ነበር የተባሉት ።



በሙስሊሙ  ማህበረሰብ የፍርድ ዉሎ ከታዩ ድራማዎች  ውስጥ  ቀን ቀጠሮ ማራዘሙ አሰልቺ የነበረ ሲሆን ፣

ምክንያቶች  መብራት የለም ፣ የመሐል ደኛው አልተገኙም  ፣  ወዘተ ምክንያቶች  አሰልቺ ነበሩ ፣ በ ተለይ

አቃቤ ህግ   ካቀረባቸው የዉሸት ምስክሮች  ሰለ አህመዲን ፣ያወሩ እና የትኛው ነው አህመዲን ሲባሉ አቡበከረን

አልያም ሌላ ግለሰብን  ያመላከቱት ነበር   ይህ የማይረሳ አስቂኝ ትዝታ ነበር ።  በአጠቃላይ የፍርድ  ውሳኔው

 ከ መጋረጃ ጀርባ የተሰጠ እና የቀረበውን  ብዛት ያላቸውን የቪዲዮ እና የጹሑፍ  መሰረጃ አይቶ በ አንድ ወር

ውስጥ ለውሳኔ የቀረበበት ሁኔታ  ፍርዱ በጀርባ ማለቁን ያሰገነዝበናል ።



የ ፍርድ ውሳኔው   !



የፍርድ ውሳኔው  የተሰጠው በ 17 የመፍትሄ አፈላላጊ ከሜቴ ላይ ብቻ ሳይሆን  በመላው የ ኢትዮጵያ  ሙስሊሙ

ማህበረሰብ ላይ ነው ፣ ጥያቄው  የመላው ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንጂ የኮሜቴው ብቻ አይደለም ፣ የታሰረው 45

ሚሊዮን  የሚጠጋው  የሙስሊሙ ማኅበረሰብ  ነው በንፁሀን ላይ የሚሰራውን ግፍ እና ስቃይ  ይብቃ !  ነፍሰ

ገዳይ  እና ወንጀለኞች  ተቀምጠው  ንፁሃን ወደ እስር የሚሄዱበት ግዜ ይብቃ  !





አርበኛ  ሰኢድ ሸልመው

ሐምሌ  2007