Sunday, March 29, 2015

የቴክኖሎጂ ነጻነት በኢትዮጵያ - ቢንያም ሙሉገትታ

የቴክኖሎጂ ነጻነት

ቢንያም ሙሉገትታ 




ወያኔ የኢንተርኔት እና ሌሎች ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን መስፋፋት ጠቃሚ እድሎች እንደሆኑ ሊቆጥራቸው ይገባል፡፡ 


የቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፉን እድገት ማበረታታት ሃገሪቱን ለማዘመን እና ትልቅ ተስፋ የተጣለበትን የኢኮኖሚ እድገት እቅድ 


ለማሳካት ወሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ዘርን  መሰረት ያደረጉ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው እና ከ20 ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ 


የሚገኘው ገዥው ወያኔ  ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን፣ የመደራጀት እና በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብቶችን እጅግ በከፍተኛ 


ሁኔታ መገደቡን ቀጥሎበታል፡፡ አፋኝ የሆኑ ህጎችን በመጠቀም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና ነፃ መገናኛ ብዙሃንን 


አጥፍቷል፤ እንዲሁም ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለባቸው ክሶችን በመመስረት ግለሰቦችን ያጠቃል፡፡ 

በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንኙነት የማድረግ፣ ሃሳባቸውን የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት ችሎታቸው 

ከሚያበረክተው ማህበራዊ ጥቅም ይልቅ በሕዝቡ ላይ ያለውን ቁጥጥር ለማስቀጠል ስፋት ባለው የክትትል እና የስለላ ስራ ላይ 

ለሚተማመነው ገዢው ፓርቲ እንደ ፖለቲካ ስጋት ምንጭ የሚታይ ሆኗል። 

ወያኔ በኢንተርኔት እና ሞባይል ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ሲሆን ይህም አገልግሎቱ ለምን ጥቅም እንደዋለ 

`ኢትዮ-ቴሌኮም በተሰኘው መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ አማካኝነት በፍጥነት እያደገ ያለውን የቴሌኮምዩኑኬሽን 

ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት ይቆጣጠራል። ይህ የመንግስት ክትትል የማድረግ አቅም ባልተገባ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል 

አለመዋሉን የሚከታተል ገለልተኛ የህግ አውጪ እና ህግ ተርጓሚ አካል በኢትዮጵያ ስለሌለ መንግስት ዘርፉን በብቸኝነት 

በመቆጣጠር ያለምንም የበላይ ቁጥጥር መረጃ የማግኘት መንገድን ለመገደብ እና ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነቶችን 

በብቃት ማፈን አስችሎታል፡

የወንጀል እንቅስቃሴዎችን፣ ሙስናን እና ሽብርተኝነትን ለመከላከል የመልዕክት ልውውጦችን ማየት እና መከታተል ህጋዊ 

የአሰራር መንገድ ቢኖረውም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚመለከት፣ሕግ ከሚፈቅደው ውጭ 

እንደማይከናወን እና የመልዕክት ልውውጦች እና የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የሚደነግግ አሰራር  እና 

መመርያ የለም። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በፍጥነት እያደገ የመጣው የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በአግባቡ እና 

ከዚህ በፊት ከነበረው እጅግ በተለየ መልኩ ሰዎች እንዲገናኙ አዲስ እድል ፈጥሯል፤ ፖለቲካዊ ውይይቶችን ለማካሄድ የሚያስችል 

ሁኔታን እና መረጃ የማግኘት መንገድን ጨምሯል፡፡ ነገርግን በርካታ ኢትዮጵያዊያን እነዚህን እድሎች ለመጠቀም አልታደሉም፡፡ 

ይልቁንም የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ህዝብን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ለማቆየት መንግስት የሚፈልገው ሌላ 

መንገድ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ይህም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመደራጀት መብቶችን በማፈን፣ ግለሰባዊ መብቶችን 

በመግፈፍ፣ የመረጃ ተደራሽነትን በመገደብ ብሎም የተለዩ ሃሳቦች እንዳይንሸራሸሩ እና ትርጉም ያለው ውይይት እና ክርክር 




እንዳይደረግባቸው ያደርጋል።

Saturday, March 28, 2015

hበኢዮዽያ የጏዳና ተዳዳሪዎች ሕዻናት - አሊ ሊበን

አሊ ሊበን                              hበኢዮዽያ የጏዳና ተዳዳሪዎች ሕዻናት
በኢትዮዾያ ውስት ቤት የለላቸው ወይም የጎዳና ተዳዳሪዎቺ ህሳናት ኩትር ከጊዜ ወደግዜ አየተባባሰ አና ኩትሩም አየጨመረ መትቶኣል።ማስታወስ ከጀመርኩበት ግዜ ጀምሮ መንገድ በቴ ሁኖኣል፤ በጎዳና ላይ በመኖሬ ኣንድም አንኩኣን መልካም ነገር ኣላገኘሁበትም ይላል የ፲፬ ቱ ኣመት ታዳጊ ወታት ማንደፍሮ ካሳ፥በወረታ ከተማ መንገድ ላይ ያደገው

   ኢትዮዽያ በኣለም በጎዳና ነዋሪዎች ህዻናት ኩትር ብዛት ከፍተኛውን ቦታ ከምዪዙት አገሮች ውስት አንዱአ ናት።13%በኢትዮዽያ የሚገኙ ህዻናቶች ኣንዱን ወዪም ሁለቱን ወላጅ በተሰቦቻቸውን ያጡ ናቸው።ዪሄም ወደ 8ነትብ 6 ሚሊኦን ኣካባቢ ዪሆናል።ከነዚህም ውስት ከሚሊኦን በላይ የሚሆኑት ወላጆቻቸውን ያቱት በኣድስ በሽታ ነው።
 ምንም አንኩኣን ከኣለም ኣከፍ ማህበረሰብ ኤድስን መስፋፋት ለመከላከል ኢትዮዽያ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ አርዳታ ብታገኝም፤በዚህ በሙስና በተጨማለከ የወያኔ ማፍያ መንጊስት ምን ያህል ገንዘብ ስራ ላይ አንደዋለ ባዪታወቅም አጂግ በታም ዝቅተኛ ሊሆን አንደሚቺል ዪገመታል።
           ልክ አንደ ማንደፍሮ ያሉ በሚሊኦን የሚቆተሩ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናቶቺ መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጅ መብት የላቸውም ልክ ትምህርት የመማር የህክምና ኣገልግሎት ማግኘት ምግብ ወዘተ።አነዚህን መሰረታዊ ነገሮቺ ለማግኘት አነዚህ ህጳናት ያለ አድሜያቸው የተለያየ ስራ ለመስራት ዪገደዳሉ በዚህም የተነሳ ለበሽታና ለተለያዩ ኣደጋዎቺ ዪጋለታሉ።
         በኣዲስ ኣበባ ፴% ኣካባቢ የሚሆኑት ልጃገረዶቺ አድሜያቸው ከ 10 አስከ 14 ያሉ  ከበተሰቦቻቸው ጋር ኣዪኖሩም። ከ ፫ ሚሊኦን በላይ የሚሆኑ ህጻናቶቺ ዛረ በኢትዮዽያ በተለያየ ምክንያት የተነሳ ኣካለ ጎደሎ ናቸው።ብዙን ጊዜ የዚህ መንስኤው የምግብ አቶት ነው።ይሄን ከፍተኛ የህሳናት ቺግር ለመቅረፍ ትቂት የመንግስት ተቆሞቺ አንዳሉ ቢታወቅም ኣስፈላጊውን ውቴት ግን ኣላመቱም።ሚክንያቱም ከደም ብየ አንደገለጽኩት ለዚህ ጉዳይ ተብሎ ከበጎ ኣድራጊዎቺ የሚገኘው ገንዘብ በሙስና ሲለሚዘረፍ ነው።
           ያለፈው ስራት መትፎ አንደነበረ ዪታወቃል።ግን ወላጅ የሊላቸውን ህሳናት በመርዳት በኩል ሲያደርግ የነበረው አንቅስቃሴ የሚረሳ ኣዪደለም።ምንም አንኩኣን ያራምደው ከነበረው ፖለቲካ ኣኳያ አንደዛሬ ከምእራብ ሃገሮቺ ብድርና እርዳታ በሌለበት ሁነታ መንግስት በየከተማው ከፍቶ በነበረው የህጳናት ኣምባ ወዪም ማሳደጊያ ኣቅም በፈከደ መተን  ለነዚህ ህጳናት መሰረታዊ የሆነ አርዳታ ያደርግ ነበር።
     ዛሬ አንደ ወያኔ ኣባባል ሃገሪቱ የ 11% አድገት አያሳየቺ፣ ከመራብ ሃገሮቺ ብድርና አርዳታ አየተደረገ በብዙ ሚሊኦን የሚቆተሩ ኢትዮዽያን ህጳናቶቺ ለዚህ ኣደጋ መጋለታቸው የሚያሳየው ምንድነው የኣንድ ሃገር ሃብቱዋ ዜጎቹዋ ናቸው።ሲለዚህ ነገ ሃገሪቱን የሚረከቡትን ታዳጊ ወታቶቺ በዚህ መልኩ አንዲያልኩ ማድረግ መልክቱ ኣንድ ብቻ ነው።ኢትዮጵያን ማትፋት ነው።ጉዳዩ ካሰብነው በላይ ነው። ሲለዚህ ነገ ሃገራቺን ከመትፋቱዋ በፊት ይህን ወንበዴ የወያኔ ቡድን ሃይላቺንን ኣስተባብረን ሳያተፋን አናትፋው አላለሁ።
      
                                ዘረኛው ወያኔ በተባበረ የህዝብ ትግል ባቺር ጊዜ ዪወድቃል። ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር።አናሸንፋለን

የግፍ እና የሰቆቃ እስር በኢትዮጵያ - ሰይድ ሽለም

የግፍ እና  የሰቆቃ  እስር  በኢትዮጵያ
ሰይድ ሽለም

ወያኔ እስር ቤቶችን  " ማረሚያ  ቤቶች" እያለ ቢጠራቸውም መጠሪያው  እውነተኛውን የእስር ቤቱን ገፅታ  ሰለማይገልፁ እንደ ቀድሞ  ስሙ "   ወህኒ  ቤት" ተብሎ ቢጠራ የተሻለ  ይመስለኛል ። የኢትዮጵያ  ወህኒ ቤቶች  ከዚህ  በፊት  ከነበሩት የከፉ  ናቸው ለማለት  ይቻላል  ። ምክኒያቱም የግፍ እና የሰቆቃ  እስሩ  እጅግ ሰብአዊነት  በጎደለው ሁኔታ በፖለቲካ  አሰተሳሰብ  እና  በዘር  ላይ  ያነጣጠረ መሆኑ ነው  ። 

የሀገራችን ግዙፍ  እስር ቤቶች  ሰነድ  እንደሚያመላክተን 90 % ያህሉ  እስረኞች  ,,,, በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመንግስት ላይ ነፍጥ  ባነሱ  ድርጅቶች  ጋር ግንኙነት  በተመለከተ  ሲሆን  ታሳሪዎቹ  የድርጅት  ተከታዮች  አሊያም  አባሎቻቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ  ደግሞ ፍፁም ከዚህ  በራቀ መልኩ እና ሁኔታ  ምንም  ግንኙነት ሳይኖራቸው  የተጠረጠሩበትን የድርጅቶቹን ስም  እንኳን የሰሙት  ከታሰሩ ቡኃላ ነው ።

በሃገራችን በሚገኙ እስር ቤቶች  ማለትም ድሬደዋ ፣ ቀሊቲ፣ ቂሎንጦ ፣ ሸዋሮቢት  እና  ዝዋይ   የፌዴራል እሰሥር ቤቶች  ተብለው ሲጠቀሱ ። ከነዚህ ውጪ የክልል እስር ቤቶች በርካታ የክልል ከተሞች  በ መሃል  አዲስ አበባ  በሚገኙ ቪላዎች  በደህንነት ተቋሞች እና ወታደራዊ  ካምፖች ውስጥ  ጭምር ስውር እስርቤቶች ተቋቁመዋል ። እንዲሁም  በርካታ በደረግ  ዘመን የሸቀጣሸቀጥ እና የእህል  መጋዘኖች ኢሕአዴግ  ወደ ስወረድ  እሥር ቤትነት  ቀይሮቸዋል ። 

ኢህአዲግ  ለዚህ እኩይ  ተግባሩ ለይመሰል  የሚያቀርባቸው የክስ መዝገቦች  : 

1 የሃገርን ግዛት  እና አንድነት መንካት ( ህገ መንግሰቱን በሃይል  ለመናድ  መሞከር  ) 

2 ሽብርተኛ  ( በ 2001 በወጣው  ሽብርተኝነት  አዋጅ  ) 

3  አርበኞች  ግንባር ፣ ኦነግ  ,,,,,,ወዘተ በሚል  ነው

በኢትዮጵያ  እሥረኞች  ላይ የሚደርሰው  እንግልትና  ድብደባ  ሰቃይ  በ 21 ክፍለ ዘመን  አለቀረም  እንዴ  ያስብላል ። የሠው ልጅ    ስጋው  ተበጣጥሶ የሚወድቅበት ፣ በጋለ ብረት የሚቃጠልበት ፣ ወንድ ልጅ እንደ እንሰሳ  የሚኮላሽበት ፣ ጥፍር የሚነቀልበት ። በእነዚህ የማሰቃያ ስፍራ  የወንድ ልጅ ብልት  የዘር ፍሬ  በሰቴኘላር ይታሰርበታል፣ ውሃ ኮሳ ይታሰርበታል ሌሎችም  ተዘርዝረው  የማያልቁ  እጅግ  ዘግናኝ  የግፍ ድርጊቶች  ይፍፀማሉ ።

ይህ ነው የሀገራችን  ዴሞክራሲ  ,,,,, ይህ ነው የሀገራችን  መልካም አስተዳደር  ያሳዝናል, ,,,,, ፍትህ ለታሰሩት ፣ ፍትህገ እና ዴሞክራሲ  በቁም  አራተኛ ለሆነው  ለመላው  ኢትዮጵያ ህዝብ ። 

አዘጋጅ አርበኛ   ሰኢድ ሸለመው 

የውሃ ምንነትና የተንዣበበበት አደጋ - እስክንድር ንጉሴ

የውሃ ምንነትና የተንዣበበበት አደጋ 

Eskender Negussie እስክንድር ንጉሴ


              ምድራችንን ህይወት የሚኖርባት ገነት ካደረግዋት ነገሮች አንዱ ውሃ ነው. ውሃ በሶስት አይነት ሁነታ የመገኘቱ ሚስጥር ህይወት እንዲቀጥል አድርጎታል. ስለውሃ ጥቅም ብዙ መዘርዘር ይቻላል በአጭሩ ግን ውሃ ከሌለ ህይወት የለም. ምድር 70%ቱ በውሃ የተሸፈነ ነው. ከዛ ሁሉ ውሃ ግን ጨዋማ ያልሆእው 1 ፐርሰንት ብቻ ነው.ከዚህ ሁሉ ውሃ 1% ብዙ ቢሆንም ከአለም ህዝብ ጋር ስናነጻጽረው ግን በጣም ጥቂት ነው. በተጨማሪም ከዚህ አንድ ፐርሰንት ውሃ ላይ 68% በከርሰ ምድር ውስጥ ሲገኝ፣ 31 ፐርሰንቱ ዳግሞ በበረዶ መልክ በ አርክቲክ እና በ አንታርቲካ ይገኛል. በርዶውም ሲቀልጥ ወደ ውቂያኖስ ውስት ይገባል. በዚህ መሰረት ከፍተኛውን ንጽሁ ውሃ ማግኘት አይችልም. በመሬት ወለል ላይ የሰው ልጅ በቀላሉ ሊያገኘው የሚችለው ውሃ አንድ ፐርሰንት ብቻ ነው. ይሀንንም አንድ ፐርሰንት ቀሪ ውሃ በወንዞች ላይ በመገደብ ውሃውን ወደ ጨዋማነት እንዲቀየር በማድረግ ብሎም ግድብ ወንዙ እንዲደር መንሳኤ ይሆናል፣ ለምሳሌ በሁቨር ግድብ እንደታየው  የመጠጡን ውሃ የበለጠ እንዲቀንስ ያደርገዋል. በዚህ መሰረት ግድብ መገደብ በድሮጊዜ ሰዎች የተጠቀሙበት አማራጭ ሲሆን ባለፈእርጀ ብዙ ችግሮች ሊያመጣ እንደሚችል ይታወቃል. ለምሳሌ ክግድቡ በታች ያሉትን በወዝ ውስጥ የሚገኙትን የህይወት ሰንሰለቶችን በመቆራረጥ ህይወትን ያተፋል. ከግድቡ በላይ የነበረውን ያየር ንብረት ተፈጥሮአዊ ሂደቱን በመለወጥ ያካባቢው ገባሬዎች የግብርና ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ያግዳቸዋል. ጉዳቱ ውሃ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውሃውም ውጪ ያሉትን ህይወቶችን ይነካል. በብዙ ግድቦች ምክንያት መኖሪያቸውን ለቀው ይሚሄዱት ሰውች ብቻ ሳይሆኑ እንሥሳቶችም ናቸው. ከዚህ በፊት እንዳልነው ግድቦች ውሃው ውስጥ ያለውን የምግብ ሰንሰለት ያጠፋሉ፣ በዚህ የተነሳ በአካባቢው የሚገኙ አሳ የሚመገቡ ወፎች አካባቢውን ለቀው ይሰደዳሉ.
                 ወደ ኢትዮጵያ ስናትርኩር የውሃ ችግር ዘመናትን ያስቆጠረ ነው ነገር ግን ኢትዮጵያ የውሃ ዓንባ ስትሃኦን ህዝቦቹዋ ውሃን ሊያገኙት እልቻሉም ለምሳሌ በሃረር ከተማ ከ25 እመታት በፊት የተከሰተው እሳሳቢ የውሃ ችግር እስካሁን መፍቴ ባለማግኘቱ እስካሁን እየተገለገሉ ያሉት ውሃ በትራንስፖርት ከእለማያ ድሬደው እንዲሁ ከእካባቢው የገጠር መንደሮች በማመላለስ ሲሆን ከተማ ውስጥ በማንኛውም ሰእት ሰዎች የ ውሃ መያዣ ይዘው ውሃ ፍለጋ ሲንከራተቱ መየት የተለመደ ነው ማንኛውም እይነት መኪና ዊሃ ወደ ከተማዋ ሲያጉጉዝ ዪስተዋላል እየባሰ የመጣው የውሃ ችግር የእለማያ ሃይቅ በመድረቁ ተባብሶ ቀጥሎል ታዲያ የሃረርን ህዝብ የየጎረበት ሃገርን የመብራት ችግር የሚፈታውን የህዳሴ ግድብ ለመገንባት ቦንድ ግዛ መባሉ እዪቀርም የቱ ቅድሚ መሆን እንዳለበት ፍርዱን ለእድማጮቼ እተዋልው
               ግብጽ በየአመት ተጨማሪ 21 ቢልዮን ኩቢክሜትር ውሃ እንደምትፈልግና ማንኛውንም በወንዙ ላይ የሚካሄደውን ግንባታ በቸልተኝነት እንደማትመለከተው የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ. 90 ሚሊየን ህዝቡዋ ወደ 150 ሚሊየን ስለሚያድግ በውሃ ላይ ያላት አቋም ከፍተኛ እንደሆነ የመስኖው ሚኒስተሩ ሆሳም ሙግዛሪል ገለጹ. ግብጽ፣ሱዳንና ኢትዮፒያ በአባይ ውሃ ላይ ደርሰውበታል የተባለውን ፍትሃዊ አጠቃቀም በከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድ ዛሬ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ይፈራረሙበታል ተብሎ ይጠበቃል. ሃገራቱ ደርሰውበታል የተባለው ፍተሃዊ አጠቃቀም ለህዝቡ ገና ይፋ አልተደረገም. ግብጽ ከአባይ ውሃ ማግኘት የሚገባትን ያህል ውሃ እያገኘች እንዳልሆነ ሚኒስተሩ ገልጸዋል. በድርድሩ የግብጽን የውሃ ፍላጎት ለማስከበር ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል. በአሁን ሰአት 55 ቢልየን ኩቢክሜትር ውሃ በየአመቱ እንደምታገኝ እና በቃጣይ አመታት ተጨማሪ ውሃ እንደሚያስፈልጋት መገለጽዋ ይታወሳል.

               ግብጽ ሱዳንና ኢትዮፒያ ግድቡ ይሚያስከትለውን ጉዳት የሚያጠና እለም እቀፍ ድርጅት ይፋ የማድረግ ስምምነቱ በማይታወቅ ምክንያት መራዘሙ ይታወቃል ሆኖም ዛረ ስምምነቱን ሲያጸድቁ አለም አቀፍ ድርጅቱን ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል. ኢትዮጵያ በቡድኑ ውስጥ አለም አቀፍ ባሉሙያ እንዲሳተፉ ፈቀደች. በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለምን አለም አቀፍ ባለሙያ እንዲካተቱት እንደፈቀዱ የሰጡት ማብራሪያ የለም.

Thursday, March 26, 2015

በውኑ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ በኢትዮጵያ በ2007 ይታሰባል ወይ? Ezra Feleke ዕዝራ ፈለቀ

Ezra Feleke   ዕዝራ ፈለቀ


 በውኑ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ይታሰባል ወይ?

በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ የተጀመረው እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ1957 በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን በ1955 የወጣውን ህገ -መንግስት መሰረት ያደረገ ንጉሱንና የላይኛውን ቤት ወይም ሴነቱን የማይመለከት ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት ኣባላትን መምረጥ ተጀምሮ ነበር። እማኞች ሲነግሩን ምርጫውና ቆጠራው ግን ሃቀኛ ነበር ኣሉ። ታዲያ ንጉሱ በነበሩበት ዘመን የነበሩት ምርጫዎች ጅማሪያቸው መልካም ቢሆንም ዓለም በማህበራዊ ለውጥ ላይ በነበረችበት በመጨረሻው ሰዓት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ህገ-መንግስታዊ ሞናርኪ ቀይሮ የፖለቲካውን ስልጣንና የህዝቡን ተሳትፎ ማስፋት ስላልተቻለ ወታደራዊ ደርግ ኣብዮቱን ኣንግቦ ብቅ ኣለ።
በዚህ ምክንያት በደርግ ዘመን የመድብለ ፓርቲ ስርዓትም ስላልነበረ ምርጫዎች ተካሄዱ ማለት ኣይቻልም።
ዓለም ወደ ዴሞክራሲ በጣም በተዘረጋችበት፣ ብዙ ኣገራት ወደ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በጣም ባደጉበት ጊዜ ወደ ስልጣን የመጣው ወያኔ መራሽ የኢህዓዴግ መንግስት ደግሞ ስልጣን ከያዘበት ከ1983 ጀምሮ ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ኣራት ምርጫዎች የተደረጉ ሲሆን ኣምስተኛው ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወር ላይ ይካሄዳል። ያለፉትን ኣራት ምርጫዎች ስናይ ሁሉም ዓለም ኣቀፍ ደረጃቸውን ያልጠበቁ በሚል የተከሰሱ፣ በተለይም የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የሰበረ፣ ስብራቱም እስካሁን ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል።
እነዚህ ኣራት ያለፉ ምርጫዎች ስለምን እክል የበዛባቸውና በጣም የሚታሙ ሆኑ? ከመሰረቱ የምርጫ ችግር ኣለ ማለት ነው? ኣሁን ለኣምስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ምርጫስ በምን ይለያል? በኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ከባቢ ኣለ ወይ? ተስፋ እናድርግ ወይ? ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ መሰረታዊ ነገሮች ምን ምን ናቸው? በነዚህ መስፈርቶች ሲመዘን በውኑ ምርጫ በኢትዮጵያ ኣለ ለመባል ያስችላል ወይ? የሚሉትን የመወያያ ኣሳቦች ኣውራጅ ኣድርገን ጥቂት ብንወያይ ደስ ይለኛል።
በውኑ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ይታሰባል ወይ? ብለን ኣጥብቀን ስንወያይ በመጀመሪያ ምርጫን ለማካሄድ ምን ምን መሰረታዊ ጉዳዮች መሟላት ኣለባቸው? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ኣንድ ሁለት ተብሎ በግልጽ መቀመጥ ኣለበት ብየ ኣመንኩ። ከዚያም ከነዚያ መስፈርቶች ኣንጻር የኢትዮጵያን ሁኔታ መገምገሙ ችግሩን በግልጽ ያሳያል ከሚል እምነት ነው። በዚህ መሰረት ዋና ዋና የምርጫ ምሰሶና ማገር ያልኳቸውን 8 ጉዳዮች እነሆ
ለኣገርኣቀፍምርጫብቁየሚያደርጉጉዳዮች
1. እምነት
2. ዋስትና
3.ብሄራዊ ማንነት
4. ታዛቢ
5. የተቋማት ነጻነት
6. ኮንስትቲየንሲ
7. የፖለቲካ ለሂቁና ፓርቲዎች
8. ካምፔን
እንግዲህ ከፍ ሲል ባነሳናቸው ነጥቦች ኣንጻር ሲታይ በኣሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ የለም ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል። ችግሮቹ መብዛታቸው ብቻ ሳይሆን በኣጠቃላይ መሰረታዊ የሆኑ የምርጫ መጫወቻዎች ፈጽመው የሉም። የሚያሳዝን ድምዳሜ ቢሆንም ምርጫ በኢትዮጵያ የለም። ዜጎችም ከምርጫ ሳጥን ለውጥን እናመጣለን ብለው በየኣምስት ኣመቱ መድከም ዋጋ የለውም።
መንግስት የምርጫን ፕሮፓጋንዳ ኣንድ የፖለቲካ የስልጣን ማራዘሚያ መሳሪያ ኣድርጎ ነው የሚያየው። ይህ መታወቅ ኣለበት። በተለይም የዓለም ባንክን፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅትንና የዓለምን ዴሞክራቲክ ኮምዩኒቲ ለመደለል ምርጫ መሳሪያ መሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል።
በኣጠቃላይ ይህ መንግስት በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ከስልጣን የሚወርድበት እድል ወደ ዜሮ የተጠጋ ሲሆን ምን ኣልባት ጥቂት ጭላንጭል የምትታየው ኣንድ ነገር ከተፈጠረ ነው። ምን ኣልባት የታጠቁ ሃይሎች ትግላቸው በርግጥ ከንድፈ ሃሳብነት ኣልፎ ማጥቃት ከጀመሩና ጫና ከፈጠሩ፣ ህዝባዊ እምቢተኝነት በየቦታው ከታየ፣ የፖለቲካ መሪዎች ትግሎችን በየፊናው የመምራት ቁርጠኝነት ካሳዩ፣ የለሂቁ ክፍፍል መጥበብ ካሳየ፣ በቅርቡ ታላቋ ብሪታኒያ እንደወሰደችው ኣቋም ሌሎች ኣገራት ከቀጠሉ፣ መንግስት ምርጫን ሰበብ ኣድርጎ ሸርተት ሊል ይችላል። እነዚህ ኣስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገፉ መጪው ምርጫ ተስፋ የሚጣልበት ኣይሆንም።በቅርቡ ታላቋ ብሪታኒያ የወሰደችው ርምጃ በርግጥ የኢትዮጵያውያንን ትግል በጅጉ የሚያግዝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በውሳኔው ፈንድቀዋል። ኢሃዴግም ከብሪታኒያ የሚያገኘው 98 ቢሊዮን ብር ነጥፎበታል። ከሌሎች የምእራብ ኣገሮችና ከኣሜሪካ ግፊቱ ከጠነከረ፣ የሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በየፊናው ከከሰሱ ጫናው ስለሚጠነክር ለኢሓዴግ የሚሻለው ኣወዳደቅ በምርጫ ስም ይሻላልና ምን ኣልባት በዚህ መንገድ ምርጫ ተስፋ ሊኖረው ይችላል።ሰላማዊ ታጋዩች በምርጫ የማያምን መንግስትን ይዘው ወደ ምርጫ የሚገቡት የህዝቡን ጉልበት ተማምነው ይመስለኛል። መንግስት እንደፈለገው ምርጫውን ኣጭበርብሮ የሰጣቸውን ጥቂት ወንበር ተቀብለው “ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል” እንደሚባለው ዝም ካሉ ይህ ሰላማዊ ትግል ኣይባልም። ሰላማዊ ትግል ማለት ወደ ምርጫ ሄዶ ምርጫው ሲዘረፍ ዝም ማለት ኣይደለም። ይሄማ የሌባ ተባባሪነት ነው። ስለዚህ መንግስት ሲያጭበረብር ህዝብን በጽናት ማታገል ከሰላማዊ ታጋዮች ይጠበቃል።
በዚህ ኣሁን ባለው የፖለቲካ ኣሰላለፍ ኢትዮጵያ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ ኣትችልም። በተለይ በገዢው ኣካባቢ ትንሽ የሃላፊነት ስሜት ቢኖር ቅድመ ውይይቶች፣ ሰነዶች፣ ዋስትናዎችና ሲስተም ሊዘረጋ ይቻል ነበር። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ስምምነቶች ካልተደረጉ የምርጫ ነገር በኢትዮጵያ የሚታሰብ ኣይሆንም።

ሙስና በሃገራችን ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው ችግር በከፊል - ገረመው አራጋው -

ገረመው አራጋው -



በዚህ 24 አመት ወያኔ ስልጣል ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ባለስጣናቱ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት አየዘረፉ ያላግባብ አንደበለፅጉ የአደባባይ ሚስጥ ነው። ይህንን ዝርፊያቸዉን አንዳሻቸው ለመፈፅም አንዲያስችላችው ስልጣን በያዙ ማግስት የሲቪል ሰርቪሱን አገልግሎት ሰጪ የሆኑትን የመንግስት ተቋማትን በኣዲስ መልክ በማዋቀርና ለዝርፊያው ምቹ የሆኑ የራሳቸውን ሰዎች በመሾም በመቅጠር በስፊው ሲዘርፉ ቆይተዋል ለዚሁም ድርጊታቸው ለሌብነት ከተዋቀሩት ተቋማት መካከል ኣንዱ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ለአብነት ይጠቀሳል። ይህ ተቋም ለሃገራችን ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ አያሌ የመንግስት አምራች ድርጅቶችን ፋብሪካዎችን የማዕድን ኢንተርፕራይዞችን ሆቴሎችን ወዘተ በማይታመን እጂግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ያለአግባብ ለወያኔ ባለሥልጣናት እና ዘመዶቻቸው እንዲሸጡና ያላግባብ እንዲበለፅጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል።

ወያኔ በፈጠረው ህዝብን ያላማከለ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አያሌ የዉጪ ባለሃብቶች ትውልደ ኢትዮጵያን እና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ወያኔን አምነው መዕዋለ ንዋያቸውን በከንቱ አፍሰው ንብረታቸውን ተቀምተው ከሃገር እንዲወጡ ተገደዋል። ለዋቤነት ያህል በጋንቤላ አካባቢ ሲካሄድ የነበረው ኢንቨስትመንት የአያል ኢትዮጵያንን ህይወት የከጠፈ በመሆኑ በአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት ባለመኖሩ ኢንቬስተሮቹ ሃገር ጥለው ለመውጣት ተገደዋል። በሌላ በኩል ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን በተሰማሩበት የኢንቨስትመንት መስክ ወያኔ የዘረጋው ቢሮክራሲና ስር የሰደደ ሙስና ለስራቸው ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸውብ በእጃቸው ያለዉን መዋዕለ-ንዋይ ጨርሰው የጀመሩትን ኢንቨስትመንት ጥለው ተማረው ከሃገር እንዲውጡ ተገደዋል። የሃገር ውስጥ ኢንቬስተሮች የሚሰማሩበትን የኢንቨስትመንት ፕሮፖሳል ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያቤት ሲያስገቡ ይህ ፕሮፖሳል አዋጪ ሆኖ ሲገኝ ለባለቤቱ አዋጪ እንዳልሆነ ምላሺ ተሰጥቶት ወያኔ ለራሱ እያዋለ ሃብትን አከማችቷል። በሌላ መልኩ አገዛዙ በዘረጋው ስር የሰደደ ሙስና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከውጪ ባለሃብቶች እና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢንቬስተሮች ማግኘት የሚገባትን መዋዕለ-ንዋይ ሳታገኝ ቀርታለች። ይባስ ብሎ ባላሃብቶች ወደ ሃገር ከሚያስገቡት የውጭ ምንዛሪ መዋዕለ -ንዋይ ይልቅ ከ ሃገራችን ወደ ሃብታም ሃገሮች በስርቆት መልክ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ መብለጡ ኣንዳንድ ጥናቶች አመላክተዋል ይህም አበዳሪ ሃገሮች በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ መሪዎች የሃገራቸውን ሃብት ወደ ውጪ እያሸሹ እኛ ለምንድ ነው ወደ ኢትዮጵያ መዋዕለ -ንዋያችንን የምናስገባው በሚል ጥያቄ አስነስቷል በስርዓቱ ላይ እምነት እንዳይጥሉበት አድርጉዋል። ሙስና በሃገራችን እንደ ተጨማሪ ታክስም ስለሆነ የግል ተቋማትና ኩባንያዎች እንዳያድጉ አድርጓል። ሙስና በሃገራችን በግል ተቋማት እና በግለሰቦች መካከል መኖር የሚገባውን ጠቃሚ ውድድር ቀንስዋል አጫጭቶታል።

በዚህ ስርዓት የተንሰራፋው ሙስና በጣት የሚቆጠሩ የወያኔ ባለስልጣናት እና ተከታዮቻቸው ካለመጠን ያካበቱት ሃብት ሕዝቡን አንዳያምኑ ስላረጋቸው ከዛሬ ነገ ሕዝቡ ይነሳብናል ብለው ስለሚሰጉ በህገወጥ ያካበቱትን ሃብትና ንብረት በማሸሽ ላይ ይገኛለ። ይህም ድርጊት ሃገር እያራቆተ ይገኛል።

በሃገራቺን የተፈጠረው ወያኔያዊ ሙስና ሕጋዊና ትክክለኛ የንግድ ተግባርን አዛብቷል የፍጆታ ዕቃዎች ትክክለኛ ዋጋ በተስተካከለ መልክ እንዳይተመን አድርጏል። የሸቀጥ ዕቃዎች እንዲያንሱ ወይም እንዲጠፉ ብሎም በጏዳ በር እንዲሸጡ መንገድ ከፍቷል የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር አድርጏል ይህም ሕዝቡን አማሮ ዜጎች እራሳቸውን እንደ ባዕድ ዜጋ እንዲቆጥሩ አድርጏል።

እንዲህ ዓይነት የሙስና ገጽ በኢትዮጵያችን በጣም የተንሠራፋ ስለሆነ ባንዳንድ ሰዎች አገላለጽ “በአገሪቱ ውስጥ ዛሬ የሚካሄደው ንግድ ከማፍያ ድርጊት የማይተናነስ ነው”። በማፍያ መልክ የሚሰራው ወንጀላዊ የንግድ አሠራር ከመብዛቱም የተነሣ በድብቅ መነገድና የጥቂቶች ብቻ መጠቃቀም ባህል ይሆናል፤ ኮንትሮባንድ ተስፋፍቷል፤ ዝርፊያ ተጧጡፏል፤ ወንበዴዎች ፈጥረዋል፤ ይባስ ብለውም ወንበዴዎች የራሣቸውን ኬላ ፈጥረዋል፤ እንዳሻቸው ይዘርፋሉ። የሚያሳዝነው ግን እነዚህን የመሰሉ ክስተቶች በሀገራችን በሰፊው እየታዩ መሆናቸው ነው።

በሃገራችን የተንሰራፋው ሙስና ዜጎች በትጋት ሰርተው ሃብታቸውን እንዳያዳብሩ ቤታቸውን እንዳያቀኑ ሃገራቸውን እንዳይገነቡ አድርጏል ወጣቱ ትውልድ ተምሮ ተመራምሮ ሃገሩንና ወገኑን ከመጥቀም ይልቅ ባቋራጭ የሚበለፅግበትን መንገድ እንዲያስብ አርጎታል።

በጣም የሚያሳዝነው የወያኔ ባለስልጣናት ይህን በሙስና የዘረፉትን ሃብት የሚያውሉት እርስ በርሳቸው በመፎካከር በድሎትና በቅምጥል ዕቃዎች ውድ በሆኑ መኪናዎች ጌጣጌጦች የቤት ማስጌጫዎች በመጠጥና በልብሶች እንዲሁም ልጆቻቸውን እጂግ ውድ በሆኑ በምዕራቡ ሃገራት በሚገኙ ትላልቅ የትምህርት ተቋማት ነው።

ይህ በጠመንጃ ሃይል ለሥልጣን የበቃው ወያኔ መንግስት ተብሎ ለስልጣን ሳይበቃ ገና ከጥንት ጀምሮ የመንግስት ተቋማት ንብረት እና ባንኮችን እየዘረፈ የቤተክርስቲያንን ቅርሶች እየሰረቀ ወደ ጎረቤት ሃገራት እያሸሸ ይቸበችብ የነበረና በሙስና እጅጉን የተጨማለቀ ስርዕት መሆኑን አመላካች ነው። ስርዕቱ ስልጣን ከተቆናጠጠም በሁዋላም በተለይ ሕዝባዊ ተቋማትን በመመዝበር እና በማዳከም ተግባር በግላጭ የተሳተፈ አገዛዝ ነው። ለአብነት የመብራት ኃይል ምሰሶዎችን በመንቀል ተግባር የተሰማሩ የራሱ ሌቦች መልሰው ለወያኔ የንግድ ተቋማት በርካሽ መቸብቸባቸው አገዛዙ ምን ያህል እንደዘቀጠ የሚያመለክት ጉልህ ተግባር ነው።

እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ በየክፍለ ሀገሩ፤ በየከተማው፤ በየንመደሩ፤ በልዩ ልዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፤ ዱሮ በመንግሥት ሥር በነበሩት አሁን ግን “ለግል ባለ ሀብቶች” በርካሽ በተቸረቸሩት ተቋማት መካካእል፤ በግል ሀብቶች መስክ፤ …።ወዘተ ከሙስና ጋር የተያያዘው ችግርና የሚደረገው ደባ ተዘርዝሮ አያልቅም። በጠመንጃ ሃይል ለሥልጣን የበቃው መንግሥት ተብዬ ለሥልጣን ሳይበቃ ገና ከጥንት ጀምሮ የቤተ፡ክርስቲያን ቅርሶቻችንን ጭምር ወደ ጎረቤት አግሮች እያወጣ ይቸረችር የነበረና በሙስና እጅጉን የተጨማለቀ ስርዓት ነው። ሕዝባዊ መንግሥት የለንምና በአገዛዙና በዘራፊ ወንበዴዎች በየቦታው የደረሱት በደሎች በቀጣይነት መዘገብና መጋለጥ አለባቸው። በአጠቃላይ የወያኔ አገዛዝ በ 24 አመታት የስልጣን ዘመኑ ባለስልጣናቱ እና ተከታዮቻቸው ከእግር ጥፍራቸው እስከ እራስ ፀጉራችው በሙስና የተዘፈቁ ለሕዝባቸው ደንታቢስ የሆኑ ፀረ ኢትዮጵያ የማፊያ ስብስብ በመሆናቸው ሃገር እና ሕዝብን ከውድቅት ለማዳን በተባበረ የህዝብ ትግል ከስልጣን መወገድ ግድ ይላል።

ወያኔ መወገዱ አይቀርም ይወገዳል እናሸንፋለን !!

ገረመው አራጋው

Sunday, March 22, 2015

Deaf Ethiopian immigrant jailed and 'refused interpreter' sues sheriff's department | Daily Mail Online

Deaf Ethiopian immigrant jailed and 'refused interpreter' sues sheriff's department | Daily Mail Online:



'via Blog this

Deaf Ethiopian immigrant jailed SIX WEEKS while being 'refused access to interpreter' sues sheriff's department

  • Abreham Zemedagegehu was jailed in Arlington County, Virginia in February 2014 and accused of stealing a man's iPad
  • He says jailers failed to meet Americans with Disabilities Act standards by refusing to provide him with an interpreter
  • The man who accused Zemedagegehu of stealing his iPad soon found it
He knew he was in jail, but he didn't know why.
Eventually, Abreham Zemedagegehu learned that he'd been accused of stealing an iPad — an iPad whose owner later found it. He spent the next six weeks in jail, unable to communicate with his jailers because he is deaf. He described a frightening, isolated experience in which medical procedures were performed without his consent and he feared for his safety.
Zemedagegehu sued the Arlington County sheriff last month in federal court, saying his treatment failed to meet the standards of the Americans with Disabilities Act.
Suing: A U.S. citizen who was born in Ethiopia, Abreham Zemedagegehu learned that he'd been accused of stealing an iPad--an iPad whose owner later found it

Suing: A U.S. citizen who was born in Ethiopia, Abreham Zemedagegehu learned that he'd been accused of stealing an iPad--an iPad whose owner later found it
'I felt like I was losing my mind,' Zemedagegehu said through an interpreter in an interview at his lawyer's office. 'I thought Virginia would give me an interpreter and they said no. That's why I felt lost.'
Zemedagegehu, who is homeless, is a U.S. citizen who was born in Ethiopia. He grew up using Ethiopian Sign Language. He has learned American Sign Language, but he has never learned more than rudimentary written English.
Maj. Susie Doyel, a spokeswoman for the sheriff's office, which runs the jail, declined to comment on the specific allegations. She generally defended the jail's ability to handle deaf inmates and others with disabilities, and said several deputies in the jail are proficient in sign language.
But she also acknowledged that communication with a deaf inmate is more problematic in cases where the inmate can't communicate in written English.
In court papers filed Monday, lawyers for the sheriff ask a judge to dismiss the case, arguing that even if Zemedagegehu's allegations are true, they fail to show intentional discrimination because they attempted various different ways to communicate with him, including handwritten notes.
And even if the discrimination were intentional, the lawyers write that it would not violate federal law because there is a rational basis for the discrimination: 'it takes extra resources and creates additional security considerations to bring in an ASL interpreter,' they write.
Zemedagegehu's ordeal began Feb. 2, 2014, as he sought a warm place to sleep at Reagan National Airport. According to Zemedagegehu's lawsuit, officers from the Metropolitan Washington Airports Authority arrested him on a complaint that he had stolen another man's iPad. 
Jailed: He spent the next six weeks in jail, unable to communicate with his jailers because he is deaf. He described a frightening, isolated experience in which medical procedures were performed without his consent and he feared for

Jailed: He spent the next six weeks in jail, unable to communicate with his jailers because he is deaf. He described a frightening, isolated experience in which medical procedures were performed without his consent and he feared for
Zemedagegehu says he requested an ASL interpreter to explain what was happening, but instead was taken to the Arlington jail for processing. He said the booking process was bewildering, with someone speaking on a video screen and he not understanding what was happening.
After he was booked, he underwent a medical screening, and says he was given forms to sign. He didn't know what they were, and refused to sign them. He says they stuck a needle in his arm without explaining what was occurring — he later learned it was tuberculosis test, to which he suffered a bad reaction.
It was not until he was arraigned Feb. 4, and a court interpreter was present, that he understood the charge against him.
When he was offered an opportunity to communicate, he said the jail provided a TTY device. Zemedagegehu said the machine was useless — it types out English text he doesn't understand, and as a practical matter, he said, no one in the deaf community still uses a TTY device. He needed instead access to a videophone or video relay service that is more commonly used, he said.
Maj. David Kidwell, director of the jail for the sheriff, also declined to comment specifically on Zemedagegehu's care, but generally defended the use of a TTY machine.
'It gets used, absolutely. It's an accepted practice, and we've had great success with it,' he said.
On March 14, 2014, Zemedagegehu struck a plea deal, pleading guilty to lesser misdemeanor charges in exchange for time served. Zemedagegehu says he only took the deal to get of jail, and that he didn't steal the iPad.
Zemedagegehu's public defender filed a motion after the guilty plea seeking to have the conviction overturned, saying prosecutors failed to turn over evidence that the man who claimed his iPad was stolen actually had found it some time before the guilty plea. Prosecutors deny withholding evidence.
A judge refused to overturn the conviction, saying the appeal had been filed too late.
 Zemedagegehu sued the Arlington County sheriff last month in federal court, saying his treatment failed to meet the standards of the Americans with Disabilities Act

 Zemedagegehu sued the Arlington County sheriff last month in federal court, saying his treatment failed to meet the standards of the Americans with Disabilities Act
Zemedagegehu said he doesn't understand why it was so difficult for the legal system to accommodate him with an interpreter.
'They're doing this 25 years after the Americans with Disabilities Act was passed. They know better,' he said.
Caroline Jackson, an attorney with the National Association of the Deaf, who is helping on Zemedagegehu's case, said cases like his are 'distressingly common. There's an assumption that persons behind bars have no rights.'
The ADA itself does not spell out exactly what kind of accommodations a jail must make for deaf inmates. But since the law was passed, several lawsuits have addressed similar issues. In 2010, the Virginia Department of Corrections reached a settlement requiring it to provide qualified interpreters during the booking process and when providing medical care, among other things.
Doyel said the county jail, which isn't part of the state prisons system, has passed audits conducted by the state Department of Corrections and has received accreditation from outside groups.
Larry Tanenbaum, a lawyer with Akin Gump, the firm that took Zemedagegehu's lawsuit on a pro bono basis, said he thinks the jail failed to meets its standards in its incarceration of his client.
'To me, it's a matter of human kindness. You see a person in your care who's lost. How do you not help him?' Tanenbaum aske


Read more: http://www.dailymail.co.uk/news/article-3002097/Deaf-immigrant-jailed-6-weeks-no-access-interpreter.html#ixzz3V7Sp3L3R
Follow us: @MailOnline on Twitter | DailyMail on Facebook

Thursday, March 19, 2015

Ethiopian pilot found guilty of hijacking plane so he could seek asylum - More World Stories News & Top Stories - The Straits Times



PUBLISHED ON MAR 18, 2015 3:20 AM
 7 188 0 0PRINTEMAIL
A screenshot from online footage of the hijacked plane at Geneva. An Ethiopian Airlines pilot who last year diverted a plane to Geneva so he could seek asylum, was on Monday convicted in absentia of hijacking the aircraft by a court in Addis Ababa, local radio reported. -- PHOTO: YOUTUBE
ADDIS ABABA (AFP) - An Ethiopian Airlines pilot who last year diverted a plane to Geneva so he could seek asylum was, on Monday, convicted in absentia of hijacking the aircraft by a court in Addis Ababa, local radio reported.
The pilot, 32-year-old Ethiopian Hailemedehin Abera Tagegn, was second in command on the flight that was carrying 202 passengers from Addis Ababa to Rome.
He locked himself in the cockpit when the captain went to the bathroom, sent a signal saying he had hijacked the plane, and diverted it to Geneva.
The Ethiopian court threw out a charge of endangering the safety of the flight since the co-pilot's actions did not put passengers or crew members in harm's way.
signupalreadymember
Sentencing will take place on Friday.
Tagegn, who had been working for the company for five years, was unarmed when he took control of the flight.
The plane landed safely in Geneva, escorted by Italian and French fighter jets.
Once on the ground, Tagegn turned off the engines, used a rope to reach the tarmac from the cockpit window and identified himself to Swiss authorities.
He said he was seeking asylum since he "felt threatened" in his country.
Swiss authorities in May rejected an Ethiopian request for Tagegn's extradition saying he would be tried in Switzerland.
Rights groups routinely accuse Ethiopia of clamping down on opposition supporters and journalists, using anti-terrorism laws to silence dissent and jail critics.
- See more at: http://www.straitstimes.com/news/world/more-world-stories/story/ethiopian-pilot-found-guilty-hijacking-plane-so-he-could-seek-as#sthash.xv6vnajc.dpuf

Sunday, March 15, 2015

Ethiopia: Gunmen kill an Ethiopian Intelligence Officer



An Intelligence Officer killed in Dagahmadow, about 160 kilometers South-East of the city of Harar
An unidentified gunmen killed an Ethiopian Intelligence Officer in Dagahmadow, the second-largest city of Degehbur Province, about 160 kilometers South-East of the city of Harar, Qorahay Media Reports.

The officer, who was in charge of the intelligence operations in an effort to crackdown the independent movement, the Ogaden National Liberation Army , was shot and killed in the middle of the night.

The agent, Abdirashid Ahmed Yare, was shot Thursday night when he was stopped on his way to house -the gunmen demanded him to leave the city with them before they kill him but he resisted.

No one is arrested in connection with the killing of the officer,  but Ethiopian Security Forces conducted house-to-house search in the city of Dagahmadow.

 No one, nor any group, claimed responsibility for the killing  Mr. Ahmed Yare. However, Ogaden National Liberation Army (ONLA) warned him three times earlier to refrain from harassing the residents of the city.

Pro-Ethiopian authority in Ogaden fears to repeat this political assassinations that are being targeted to Ethiopian Security and Intelligence officers. 

Ahmed Yare was known to fierce or vicious behavior toward the local Somali people in Ogaden region. He was a close-friend for the Ethiopian Generals. Residents of  Dagahmadow regard his void as a breakthrough.

Over the last six weeks the fight between Ogaden National Liberation Army and Ethiopian Security Forces escalated after an ONLF Commander, Mustafe Haybe, killed in action. ONLA claimed to have killed 120 Ethiopian Soldiers.

Kenya-brokered peace talks between the Tigray-ruled Ethiopian government and the ONLF is due to resume in Nairobi, Kenya again. 

ONLF Chief negotiator, Abdirahman Mahdi, who met Ethiopian delegation led-by Ethiopian Defense Minister Siraj Fegessa  to pave the way for the third-round peace talks had said in a YouTube video that they agreed each other the key principles of the preliminary talks except a point delayed for more discussions