Sunday, March 29, 2015

የቴክኖሎጂ ነጻነት በኢትዮጵያ - ቢንያም ሙሉገትታ

የቴክኖሎጂ ነጻነት

ቢንያም ሙሉገትታ 
ወያኔ የኢንተርኔት እና ሌሎች ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን መስፋፋት ጠቃሚ እድሎች እንደሆኑ ሊቆጥራቸው ይገባል፡፡ 


የቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፉን እድገት ማበረታታት ሃገሪቱን ለማዘመን እና ትልቅ ተስፋ የተጣለበትን የኢኮኖሚ እድገት እቅድ 


ለማሳካት ወሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ዘርን  መሰረት ያደረጉ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው እና ከ20 ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ 


የሚገኘው ገዥው ወያኔ  ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን፣ የመደራጀት እና በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብቶችን እጅግ በከፍተኛ 


ሁኔታ መገደቡን ቀጥሎበታል፡፡ አፋኝ የሆኑ ህጎችን በመጠቀም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና ነፃ መገናኛ ብዙሃንን 


አጥፍቷል፤ እንዲሁም ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለባቸው ክሶችን በመመስረት ግለሰቦችን ያጠቃል፡፡ 

በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንኙነት የማድረግ፣ ሃሳባቸውን የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት ችሎታቸው 

ከሚያበረክተው ማህበራዊ ጥቅም ይልቅ በሕዝቡ ላይ ያለውን ቁጥጥር ለማስቀጠል ስፋት ባለው የክትትል እና የስለላ ስራ ላይ 

ለሚተማመነው ገዢው ፓርቲ እንደ ፖለቲካ ስጋት ምንጭ የሚታይ ሆኗል። 

ወያኔ በኢንተርኔት እና ሞባይል ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ሲሆን ይህም አገልግሎቱ ለምን ጥቅም እንደዋለ 

`ኢትዮ-ቴሌኮም በተሰኘው መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ አማካኝነት በፍጥነት እያደገ ያለውን የቴሌኮምዩኑኬሽን 

ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት ይቆጣጠራል። ይህ የመንግስት ክትትል የማድረግ አቅም ባልተገባ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል 

አለመዋሉን የሚከታተል ገለልተኛ የህግ አውጪ እና ህግ ተርጓሚ አካል በኢትዮጵያ ስለሌለ መንግስት ዘርፉን በብቸኝነት 

በመቆጣጠር ያለምንም የበላይ ቁጥጥር መረጃ የማግኘት መንገድን ለመገደብ እና ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነቶችን 

በብቃት ማፈን አስችሎታል፡

የወንጀል እንቅስቃሴዎችን፣ ሙስናን እና ሽብርተኝነትን ለመከላከል የመልዕክት ልውውጦችን ማየት እና መከታተል ህጋዊ 

የአሰራር መንገድ ቢኖረውም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚመለከት፣ሕግ ከሚፈቅደው ውጭ 

እንደማይከናወን እና የመልዕክት ልውውጦች እና የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የሚደነግግ አሰራር  እና 

መመርያ የለም። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በፍጥነት እያደገ የመጣው የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በአግባቡ እና 

ከዚህ በፊት ከነበረው እጅግ በተለየ መልኩ ሰዎች እንዲገናኙ አዲስ እድል ፈጥሯል፤ ፖለቲካዊ ውይይቶችን ለማካሄድ የሚያስችል 

ሁኔታን እና መረጃ የማግኘት መንገድን ጨምሯል፡፡ ነገርግን በርካታ ኢትዮጵያዊያን እነዚህን እድሎች ለመጠቀም አልታደሉም፡፡ 

ይልቁንም የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ህዝብን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ለማቆየት መንግስት የሚፈልገው ሌላ 

መንገድ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ይህም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመደራጀት መብቶችን በማፈን፣ ግለሰባዊ መብቶችን 

በመግፈፍ፣ የመረጃ ተደራሽነትን በመገደብ ብሎም የተለዩ ሃሳቦች እንዳይንሸራሸሩ እና ትርጉም ያለው ውይይት እና ክርክር 
እንዳይደረግባቸው ያደርጋል።

No comments:

Post a Comment