Thursday, March 26, 2015

ሙስና በሃገራችን ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው ችግር በከፊል - ገረመው አራጋው -

ገረመው አራጋው -



በዚህ 24 አመት ወያኔ ስልጣል ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ባለስጣናቱ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት አየዘረፉ ያላግባብ አንደበለፅጉ የአደባባይ ሚስጥ ነው። ይህንን ዝርፊያቸዉን አንዳሻቸው ለመፈፅም አንዲያስችላችው ስልጣን በያዙ ማግስት የሲቪል ሰርቪሱን አገልግሎት ሰጪ የሆኑትን የመንግስት ተቋማትን በኣዲስ መልክ በማዋቀርና ለዝርፊያው ምቹ የሆኑ የራሳቸውን ሰዎች በመሾም በመቅጠር በስፊው ሲዘርፉ ቆይተዋል ለዚሁም ድርጊታቸው ለሌብነት ከተዋቀሩት ተቋማት መካከል ኣንዱ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ለአብነት ይጠቀሳል። ይህ ተቋም ለሃገራችን ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ አያሌ የመንግስት አምራች ድርጅቶችን ፋብሪካዎችን የማዕድን ኢንተርፕራይዞችን ሆቴሎችን ወዘተ በማይታመን እጂግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ያለአግባብ ለወያኔ ባለሥልጣናት እና ዘመዶቻቸው እንዲሸጡና ያላግባብ እንዲበለፅጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል።

ወያኔ በፈጠረው ህዝብን ያላማከለ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አያሌ የዉጪ ባለሃብቶች ትውልደ ኢትዮጵያን እና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ወያኔን አምነው መዕዋለ ንዋያቸውን በከንቱ አፍሰው ንብረታቸውን ተቀምተው ከሃገር እንዲወጡ ተገደዋል። ለዋቤነት ያህል በጋንቤላ አካባቢ ሲካሄድ የነበረው ኢንቨስትመንት የአያል ኢትዮጵያንን ህይወት የከጠፈ በመሆኑ በአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት ባለመኖሩ ኢንቬስተሮቹ ሃገር ጥለው ለመውጣት ተገደዋል። በሌላ በኩል ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን በተሰማሩበት የኢንቨስትመንት መስክ ወያኔ የዘረጋው ቢሮክራሲና ስር የሰደደ ሙስና ለስራቸው ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸውብ በእጃቸው ያለዉን መዋዕለ-ንዋይ ጨርሰው የጀመሩትን ኢንቨስትመንት ጥለው ተማረው ከሃገር እንዲውጡ ተገደዋል። የሃገር ውስጥ ኢንቬስተሮች የሚሰማሩበትን የኢንቨስትመንት ፕሮፖሳል ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያቤት ሲያስገቡ ይህ ፕሮፖሳል አዋጪ ሆኖ ሲገኝ ለባለቤቱ አዋጪ እንዳልሆነ ምላሺ ተሰጥቶት ወያኔ ለራሱ እያዋለ ሃብትን አከማችቷል። በሌላ መልኩ አገዛዙ በዘረጋው ስር የሰደደ ሙስና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከውጪ ባለሃብቶች እና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢንቬስተሮች ማግኘት የሚገባትን መዋዕለ-ንዋይ ሳታገኝ ቀርታለች። ይባስ ብሎ ባላሃብቶች ወደ ሃገር ከሚያስገቡት የውጭ ምንዛሪ መዋዕለ -ንዋይ ይልቅ ከ ሃገራችን ወደ ሃብታም ሃገሮች በስርቆት መልክ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ መብለጡ ኣንዳንድ ጥናቶች አመላክተዋል ይህም አበዳሪ ሃገሮች በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ መሪዎች የሃገራቸውን ሃብት ወደ ውጪ እያሸሹ እኛ ለምንድ ነው ወደ ኢትዮጵያ መዋዕለ -ንዋያችንን የምናስገባው በሚል ጥያቄ አስነስቷል በስርዓቱ ላይ እምነት እንዳይጥሉበት አድርጉዋል። ሙስና በሃገራችን እንደ ተጨማሪ ታክስም ስለሆነ የግል ተቋማትና ኩባንያዎች እንዳያድጉ አድርጓል። ሙስና በሃገራችን በግል ተቋማት እና በግለሰቦች መካከል መኖር የሚገባውን ጠቃሚ ውድድር ቀንስዋል አጫጭቶታል።

በዚህ ስርዓት የተንሰራፋው ሙስና በጣት የሚቆጠሩ የወያኔ ባለስልጣናት እና ተከታዮቻቸው ካለመጠን ያካበቱት ሃብት ሕዝቡን አንዳያምኑ ስላረጋቸው ከዛሬ ነገ ሕዝቡ ይነሳብናል ብለው ስለሚሰጉ በህገወጥ ያካበቱትን ሃብትና ንብረት በማሸሽ ላይ ይገኛለ። ይህም ድርጊት ሃገር እያራቆተ ይገኛል።

በሃገራቺን የተፈጠረው ወያኔያዊ ሙስና ሕጋዊና ትክክለኛ የንግድ ተግባርን አዛብቷል የፍጆታ ዕቃዎች ትክክለኛ ዋጋ በተስተካከለ መልክ እንዳይተመን አድርጏል። የሸቀጥ ዕቃዎች እንዲያንሱ ወይም እንዲጠፉ ብሎም በጏዳ በር እንዲሸጡ መንገድ ከፍቷል የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር አድርጏል ይህም ሕዝቡን አማሮ ዜጎች እራሳቸውን እንደ ባዕድ ዜጋ እንዲቆጥሩ አድርጏል።

እንዲህ ዓይነት የሙስና ገጽ በኢትዮጵያችን በጣም የተንሠራፋ ስለሆነ ባንዳንድ ሰዎች አገላለጽ “በአገሪቱ ውስጥ ዛሬ የሚካሄደው ንግድ ከማፍያ ድርጊት የማይተናነስ ነው”። በማፍያ መልክ የሚሰራው ወንጀላዊ የንግድ አሠራር ከመብዛቱም የተነሣ በድብቅ መነገድና የጥቂቶች ብቻ መጠቃቀም ባህል ይሆናል፤ ኮንትሮባንድ ተስፋፍቷል፤ ዝርፊያ ተጧጡፏል፤ ወንበዴዎች ፈጥረዋል፤ ይባስ ብለውም ወንበዴዎች የራሣቸውን ኬላ ፈጥረዋል፤ እንዳሻቸው ይዘርፋሉ። የሚያሳዝነው ግን እነዚህን የመሰሉ ክስተቶች በሀገራችን በሰፊው እየታዩ መሆናቸው ነው።

በሃገራችን የተንሰራፋው ሙስና ዜጎች በትጋት ሰርተው ሃብታቸውን እንዳያዳብሩ ቤታቸውን እንዳያቀኑ ሃገራቸውን እንዳይገነቡ አድርጏል ወጣቱ ትውልድ ተምሮ ተመራምሮ ሃገሩንና ወገኑን ከመጥቀም ይልቅ ባቋራጭ የሚበለፅግበትን መንገድ እንዲያስብ አርጎታል።

በጣም የሚያሳዝነው የወያኔ ባለስልጣናት ይህን በሙስና የዘረፉትን ሃብት የሚያውሉት እርስ በርሳቸው በመፎካከር በድሎትና በቅምጥል ዕቃዎች ውድ በሆኑ መኪናዎች ጌጣጌጦች የቤት ማስጌጫዎች በመጠጥና በልብሶች እንዲሁም ልጆቻቸውን እጂግ ውድ በሆኑ በምዕራቡ ሃገራት በሚገኙ ትላልቅ የትምህርት ተቋማት ነው።

ይህ በጠመንጃ ሃይል ለሥልጣን የበቃው ወያኔ መንግስት ተብሎ ለስልጣን ሳይበቃ ገና ከጥንት ጀምሮ የመንግስት ተቋማት ንብረት እና ባንኮችን እየዘረፈ የቤተክርስቲያንን ቅርሶች እየሰረቀ ወደ ጎረቤት ሃገራት እያሸሸ ይቸበችብ የነበረና በሙስና እጅጉን የተጨማለቀ ስርዕት መሆኑን አመላካች ነው። ስርዕቱ ስልጣን ከተቆናጠጠም በሁዋላም በተለይ ሕዝባዊ ተቋማትን በመመዝበር እና በማዳከም ተግባር በግላጭ የተሳተፈ አገዛዝ ነው። ለአብነት የመብራት ኃይል ምሰሶዎችን በመንቀል ተግባር የተሰማሩ የራሱ ሌቦች መልሰው ለወያኔ የንግድ ተቋማት በርካሽ መቸብቸባቸው አገዛዙ ምን ያህል እንደዘቀጠ የሚያመለክት ጉልህ ተግባር ነው።

እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ በየክፍለ ሀገሩ፤ በየከተማው፤ በየንመደሩ፤ በልዩ ልዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፤ ዱሮ በመንግሥት ሥር በነበሩት አሁን ግን “ለግል ባለ ሀብቶች” በርካሽ በተቸረቸሩት ተቋማት መካካእል፤ በግል ሀብቶች መስክ፤ …።ወዘተ ከሙስና ጋር የተያያዘው ችግርና የሚደረገው ደባ ተዘርዝሮ አያልቅም። በጠመንጃ ሃይል ለሥልጣን የበቃው መንግሥት ተብዬ ለሥልጣን ሳይበቃ ገና ከጥንት ጀምሮ የቤተ፡ክርስቲያን ቅርሶቻችንን ጭምር ወደ ጎረቤት አግሮች እያወጣ ይቸረችር የነበረና በሙስና እጅጉን የተጨማለቀ ስርዓት ነው። ሕዝባዊ መንግሥት የለንምና በአገዛዙና በዘራፊ ወንበዴዎች በየቦታው የደረሱት በደሎች በቀጣይነት መዘገብና መጋለጥ አለባቸው። በአጠቃላይ የወያኔ አገዛዝ በ 24 አመታት የስልጣን ዘመኑ ባለስልጣናቱ እና ተከታዮቻቸው ከእግር ጥፍራቸው እስከ እራስ ፀጉራችው በሙስና የተዘፈቁ ለሕዝባቸው ደንታቢስ የሆኑ ፀረ ኢትዮጵያ የማፊያ ስብስብ በመሆናቸው ሃገር እና ሕዝብን ከውድቅት ለማዳን በተባበረ የህዝብ ትግል ከስልጣን መወገድ ግድ ይላል።

ወያኔ መወገዱ አይቀርም ይወገዳል እናሸንፋለን !!

ገረመው አራጋው

No comments:

Post a Comment