የግፍ እና የሰቆቃ እስር በኢትዮጵያ
ሰይድ ሽለምወያኔ እስር ቤቶችን " ማረሚያ ቤቶች" እያለ ቢጠራቸውም መጠሪያው እውነተኛውን የእስር ቤቱን ገፅታ ሰለማይገልፁ እንደ ቀድሞ ስሙ " ወህኒ ቤት" ተብሎ ቢጠራ የተሻለ ይመስለኛል ። የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት የከፉ ናቸው ለማለት ይቻላል ። ምክኒያቱም የግፍ እና የሰቆቃ እስሩ እጅግ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ በፖለቲካ አሰተሳሰብ እና በዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው ።
የሀገራችን ግዙፍ እስር ቤቶች ሰነድ እንደሚያመላክተን 90 % ያህሉ እስረኞች ,,,, በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመንግስት ላይ ነፍጥ ባነሱ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በተመለከተ ሲሆን ታሳሪዎቹ የድርጅት ተከታዮች አሊያም አባሎቻቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ፍፁም ከዚህ በራቀ መልኩ እና ሁኔታ ምንም ግንኙነት ሳይኖራቸው የተጠረጠሩበትን የድርጅቶቹን ስም እንኳን የሰሙት ከታሰሩ ቡኃላ ነው ።
በሃገራችን በሚገኙ እስር ቤቶች ማለትም ድሬደዋ ፣ ቀሊቲ፣ ቂሎንጦ ፣ ሸዋሮቢት እና ዝዋይ የፌዴራል እሰሥር ቤቶች ተብለው ሲጠቀሱ ። ከነዚህ ውጪ የክልል እስር ቤቶች በርካታ የክልል ከተሞች በ መሃል አዲስ አበባ በሚገኙ ቪላዎች በደህንነት ተቋሞች እና ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ጭምር ስውር እስርቤቶች ተቋቁመዋል ። እንዲሁም በርካታ በደረግ ዘመን የሸቀጣሸቀጥ እና የእህል መጋዘኖች ኢሕአዴግ ወደ ስወረድ እሥር ቤትነት ቀይሮቸዋል ።
ኢህአዲግ ለዚህ እኩይ ተግባሩ ለይመሰል የሚያቀርባቸው የክስ መዝገቦች :
1 የሃገርን ግዛት እና አንድነት መንካት ( ህገ መንግሰቱን በሃይል ለመናድ መሞከር )
2 ሽብርተኛ ( በ 2001 በወጣው ሽብርተኝነት አዋጅ )
3 አርበኞች ግንባር ፣ ኦነግ ,,,,,,ወዘተ በሚል ነው
በኢትዮጵያ እሥረኞች ላይ የሚደርሰው እንግልትና ድብደባ ሰቃይ በ 21 ክፍለ ዘመን አለቀረም እንዴ ያስብላል ። የሠው ልጅ ስጋው ተበጣጥሶ የሚወድቅበት ፣ በጋለ ብረት የሚቃጠልበት ፣ ወንድ ልጅ እንደ እንሰሳ የሚኮላሽበት ፣ ጥፍር የሚነቀልበት ። በእነዚህ የማሰቃያ ስፍራ የወንድ ልጅ ብልት የዘር ፍሬ በሰቴኘላር ይታሰርበታል፣ ውሃ ኮሳ ይታሰርበታል ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ እጅግ ዘግናኝ የግፍ ድርጊቶች ይፍፀማሉ ።
ይህ ነው የሀገራችን ዴሞክራሲ ,,,,, ይህ ነው የሀገራችን መልካም አስተዳደር ያሳዝናል, ,,,,, ፍትህ ለታሰሩት ፣ ፍትህገ እና ዴሞክራሲ በቁም አራተኛ ለሆነው ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ።
አዘጋጅ አርበኛ ሰኢድ ሸለመው
No comments:
Post a Comment